የጥምር 12 ኮዬ ፈጬ2 ሎት1 የመንገድ ፕሮጀክት 17.8 ኪ.ሜትር የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በኮዬ ፍጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ 5ፕሮጀከቶችን በተለያዩ የስራ ተቋራጮች እያስገባ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካካል ከ711.7 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የጥምር12 ኮዬ ፍጬ2 ሎት1 የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡
የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው IFH የስራ ተቋራጭ ሲሆን ሲቪል ወርከር ኮንሰልቲግ ኢንጂነርስ ፔሊሲ ደግሞ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እየተከታተለው ይገኛል፡፡
ይህ የመንገድ ግንባታ የአስፋልት እና የኮብል መንገድ ጨምሮ 17.8 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ10 እስከ 20 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት አለው፡፡
አሁን ላይ የከርቭስቶን ፣ የሰቤዝ ፣ የድጋፍ ግንብ ግንባታ እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ይሁን እንጂ የወሰን ማስከበር ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው ግንባታው በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅእኖ አሳድረዋል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity