የአጉስታ – ወይራ ሰፈር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፋልት ማንጠፍ ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በተለምዶ አውግስታ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እስከ ወይራ መጋጠሚያ ድረስ ተሻሽሎ እየተገነባ የሚገኘው አቋራጭ የመንገድ ፕሮጀክት አስፋልት የማንጠፍ ስራ ተጀምሯል፡፡
አሁን ላይ የመንገድ ፕሮጀክቱ ካለው አጠቃላይ 1.5 ኪ.ሜ ውስጥ 600 ሜትር የሚሆነው የአስፋልት ንጣፍ ስራ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ቀሪው የመንገዱ ክፍል ደግሞ የሰብ ቤዝ ፣ የከርቭ ስቶን፣የእግረኛ መንገድ፣ የማንሆል እና የሙሌት ስራዎች በፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህን የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥም የግንባታ ስራውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱን ግንባታ ቲኤን ቲ ኮንስትራክሽን /TNT construction / ከ308.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየገነባው የሚገኝ ሲሆን ኦሜጋ ኮንሰልቲንግ የተባለ አማካሪ ደርጅት ደግሞ የማማከር እና የቁጥጥሩን ስራ እየተከታተለው
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity