ከጀሞ 3 ወደ ቫርኔሮ አደባባይ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ ጥገና ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጀሞ3 አደባባይ እና በተለምዶ ቫርኔሮ አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአስፋልት መንገድ ጥገና አካሂዷል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ከአስፋልት ጥገና ሥራው በተጨማሪ ከአካባቢው መኖሪያ ቤቶች፣ ከፋብሪካዎችና ከሆቴሎች በሚወጣ ፍሳሽ ቆሻሻ ሳቢያ የድሬነጅ መስመር በመዝጋቱ ወደ አስፋልት የሚወጣው ፍሳሽ መንገዱን ለብልሽት በመዳረጉ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የድሬነጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ስራም አከናውኗል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity