+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የተደራሽ መንገድ ግንባታ ስራዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከዋና እና መጋቢ የመንገዶች ግንባታ ሥራዎች በተጨማሪ በአዳዲስ የመኖሪያ መንደሮች እና የመንገድ መሠረተ ልማት ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች የመቃረቢያ መንገዶች ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ደረጃ የተደራሽ መንገድ ግንባታ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ቃጥላ ማሪያም ዶሮ እርባታ አካባቢ የሚጠቀስ ነው፡፡ በዚህ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው መዳረሻ መንገድ በአጠቃላይ 430 ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ነው፡፡

በአካባቢው እየተሰራ የሚገኘው ተደራሽ መንገድ ሲጠናቀቅ በዋናነት በዶሮ እርባታ ለሚተዳደሩ ማህበራት እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ እንዲጎለብት ያግዛል፡፡

አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.