+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የአፍሪካ ህንፃ – መስታወት ፋብሪካ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት የግንባታ አፈፃፀም 80 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6 ቀን 2015 ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ጀሞ ሚካኤል አከባቢ እየገነባው የሚገኘውና ከአፍሪካ ህንፃ ወደ መስታወት ፋብሪካ የሚያገናኘው የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም 80 በመቶ ደርሶል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 1.68 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን፣ አሁን ላይ ከአጠቃላይ የፕሮጀክቱ ርዝመት 1 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የመንገዱ ክፍል ሙሉ በሙሉ የአስፋልት ማንጠፍ ስራው ተጠናቋል፡፡ በቀሪው የመንገዱ ክፍል ላይም የሰብ ቤዝ እና ተያያዥ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በመንገድ ፕሮጄክቱ ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውና 40 ሜትር ርዝመት እና 3 ሜትር የጎን ስፋት ያለውን የድልድይ ግንባታ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ በዋናነት በጀሞ መንገድ ላይ ያለውን የትራፊክ መጭናነቅ በማቃለል ከጀሞ ሚካኤል የትራፊክ መብራት በመሻገር በስተቀኝ ታጥፈው ቀጥታ ወደ ለቡ እና ፉሪ አካባቢ ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አቋራጭ መንገድ ሆኖ የሚያገለግል ከመሆኑም ባሻገር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.