+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለስልጣኑ 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን የመንገዶች ጥገና እና ማስዋብ ስራ አከናውኗ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የተለያዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ከማከናወኑም በተጨማሪ የመንገድ ዳር መብራቶችን በደማቅ ብርሀንና ልዩ ልዩ ህብረ ቀለማት ባላቸው መብራቶች የማስዋብና የማስጌጥ ስራዎች አከናውኗል፡፡

ባለስልጣኑ በተለይም ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ – በመስቀል አደባባይ – አራት ኪሎ ቤተመንግስት፣ ከካሳንችስ – ብሄራዊ- ሜክሲኮ እስከ አፍሪካህብረት ዋና ጽ/ቤት ድረስ ባለው መንገድ ላይ የፖት ሆል ጥገና፣ 40 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የከርቭስቶን ቀለም ቅብ ፣ የመንገድ ዳር መብራቶችን የመጠገን እና የድሬነጅ መስመር ፅዳት ስራዎችን በልዩ ሁኔታ አከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.