የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ግንባታ በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ጥር 27 ቀን 2015 ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በራሱ አቅም በከተማዋ እየገነባቸው ካሉ በርካታ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በተሻለ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራስ ሃይል እየገነባው ያለው ይህ የቀጨኔ ቁስቋም የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ ርዝመቱ 1.4 ኪሎ ሜትር ሲሆን 16 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡ ፕሮጀክቱ ከቀጨኔ መስመር ተነስቶ ሽሮ ሜዳ ቁስቋም የሚገናኝ ሲሆን ግንባታው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ይቀርፋል ተብሎ ይገመታል፡፡
ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል 800 ሜትሩ አስፋልት የለበሰ ሲሆን ቀሪው የቤዝ ኮርስ የእግረኛ መንገድ እና ከርቭ ስቶን ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ 260 ሜትር የሚሆነው የመንገድ ፕሮጀክት ክፍል ላይ በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራ ለማከናወን አሉታዊ ጫና አሳድሯል ፡፡
የመንገድ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ባለስልጣኑ መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity