ባለፉት 6 ወራት በጋራ መኖሪያ ቤቶች 7.51 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ ተከናውኗል
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ባለፉት ስድስት ወራት በ20/80 እና በ40/60 በጋራ መኖሪያ ቤቶች 7.51 ኪ.ሜ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ስራ አከናውኗል፡፡
በግማሽ ዓመቱ 4.52 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ እና 3.18 ኪ.ሜ የአስፋልት በድምሩ 7.7 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለመገንባት አቅዶ 7.51 ኪ.ሜ በመገንባት የዕቅዱን 98 በመቶ አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡
ባለስልጠኑ በጀት ዓመቱ በከተማዋ የተለያዩ ማዕዘናት በ40/60 እና 20/80 የቤት ልማት ፕሮግራም በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአጠቃላይ 19.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአስፋልት እና በኮብል ንጣፍ ለመሸፈን 15 ፕሮጀክቶችን በስራ ተቋራጮች እያስገነባ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል ኮዬ ፌጬ 2 መንገድ ግንባታ ሎት 1፣ ኮዬ ፌጬ 2 ፕሮጀክት 11 እና በሻሌ ኮንዶሚኒየም አስፋልት መንገድ ጥሩ አፈፃፀም ካላቻው ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity