+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ወራት ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የግንባታ ግብዓቶችን አመረተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ግብዓት ምርቶችን በማምረት ጥቅም ላይ አውሏል፡፡

ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ወራት ካመረታቸው የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች መካከል፤ 74.6 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የካባ ምርቶች፣ 47.53 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የሲሚንቶ ውጤቶች እና 58.22 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአስፋልት ኮንክሪት ምርት ይገኝበታል፡፡ በራሱ ዓቅም አምርቶ ለተለያዩ የግንባታና ጥገና ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል፡፡

ባለሥልጣኑ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ግብዓቶችን በራስ አቅም ማምረት መቻሉ፣ በግብዓት እጥረት ምክንያት የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች መጓተት እንዳይፈጠር ከማገዙም በተጨማሪ በራስ ኃይል የሚከናወኑ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች በተመጣጣኝ ወጪ እንዲፈፀሙ አስችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.