+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለባለስልጣኑ ባለ ሙያዎች የግራውንድ ፔኔትሬቲንግ ራዳር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23/2015 ዓም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በመንገድ ግንባታ ስራ ወቅት መረጃን ለመሰብሰብ የሚያስችል ግራውንድ ፔነትሬቲንግ ራዳር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ያደረገ የተግባር እና የፅንሰ ሃሳብ ስልጠና ለባለሙያዎች ሰጠ፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበዜ ሱሌማን ስልጠናው በዋናነት ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በተለያዩ የመንገድ ግንባታስራ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች በመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ እና ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚረዳ የተግባር ስልጠና ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወ/ሮ አበዜ አክለውም ባለሙያዎቹ የተሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመጠቀም የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ከማንኛውም ጉዳት በመጠበቅ ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኮሚዩኒኬሽን ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ባለሙያ አቶ ኤፍሬም ተሻለ በቅድመ ግንባታ፣በግንባታ ወቅት እና ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ መንገዶችን ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ለመመርመር እና በጥንቃቄ ለመፈተሽ የሚረዳ ተክኖሎጂ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናው በአጠቃላይ ግራውንድ ፔኔትሬቲንግ ራዳር ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በተመለከተ በፅንሰ ሀሳብ ደረጃ እና በተግባር ከተለያዩ ተቋማት ተሞክሮ በመውሰድ በዝርዝር ቀርቦል፡፡

በመሰረተ ልማቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን መሬት ሳይቆፈር ሞገድን ተጠቅሞ በመሬት ውስጥ የተደበቁ ነገሮች ለማወቅም ሆነ ለመፈተሸ የሚረዳ ተክኖሎጂ መሆኑን የገለፁት አቶ ኤፍሬም ቴክኖሎጂውን በተግባር ላይ እንዲውል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.