+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የኬላ ፈረንሳይ- ፈረንሳይ አቦ ቤተ ክርስትያን አስፋል መንገድ ፕሮጀክት የድልድይ ኮንክሪት ሙሌት ስራ በመጠናቀቀ ላይ ነው

አዲስ አበባ፡- ጥር 12 ቀን 2015 ፣ የኬላ ፈረንሳይ- ፈረንሳይ አቦ ቤተ ክርስትያን ድረስ እየተገነባ የሚገኘው የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክት አንዱ አካል የሆነው የድልድይ ግንባታ የስላቭ ኮንክሪት ሙሌት ሰራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ድልድዩ 12 ሜትር ርዝመት ፣35 ሜትር የጎን ስፋት እና 8 ሜትር ቁመት ያለዉ ሲሆን የግንባታ ስራውም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ሃይል መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ፕሮጀክት አጠቃላይ 1.2 ኪ.ሜትር ርዝመት በ15 ሜትር የጎን ስፋት እየተገነባ የሚገኝ አቋራጭ መንገድ ነው፡፡ አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል ውስጥ 700 ሜትር የሚሆነዉን አስፋልት የማልበስ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን የእግረኛ መንገድ፣ የድጋፍ ግንብ እና ቀሪ ተያያዥ ስራዎችም ጎን ለጎን እየተከናወኑ ይገኛሉ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.