+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በ6 ወራት ውስጥ 411.94 ኪሎ ሜትር የግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 12 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት ውስጥ 442 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የግንባታና የጥገና ስራዎችን ለመስራት አቅዶ 411.94 ኪ.ሜ በማከናወን የእቅዱን 93.2 በመቶ ለማሳካት ችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ውስጥ ከተከናወኑት የግንባታ ስራዎች መካከል 14 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 4.68 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 4.42 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ 18.99 ኪ.ሜ የኮብል ንጣፍ፣ 8.14 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ፣ 0.6 ኪ.ሜ የዲሬኔጅ መስመሮች እና 0.72 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ስራዎችን የሚያካትት ሲሆን በድምሩም 51.55 ኪ.ሜ ይሸፍናሉ፡፡

በተመሳሳይ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 39 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 266.3 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳትና ጥገና፣ 18.68 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድ፣ 4.36 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራ፣2.56 የእግረኛ መንገድ መከለያ አጥር እና 19.43 ኪ.ሜ የመንገድ ቀለም ስራ በማከናወን በጠቅላላው 360 ኪ.ሜ የሚሆን ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በግማሽ ዓመት ውስጥ ለማከናወን ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም 7 ሺ 795 የመብራትና አምፖል ጥገና ስራዎች በግማሽ ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.