የካርል አደባባይ በትራፊክ መብራት ሊቀየር ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከተማ ከብስራተ ገብርኤል ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የካርል አደባባይ የትራፊክ ፍሰቱን የበለጠ ለማሳለጥ ወደ ትራፊክ ሲግናል መብራት ሊቀየር ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አሁን ላይ በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨነናቅ ችግር ለመፍታት የካርል አደባባይን ወደ ትራፊክ መብራት ለመቀየር ዛሬ ምሽት የግንባታ ስራ ጀምሯል፡፡
ከሰብዓዊነት በመነጨ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ በኢትዮጵያውያን ልቦና ሲዘከር ለሚኖረው ሚስተር ካርል ሄንዝ በም መታሰቢያ መንገድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚወስነው መሠረት የሚሰየም ይሆናል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የግንባታ ስራውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን፣ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ድረስ አሽከርካሪዎች ተለዋጭ መንገዶችን በመጠቀም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ያሳስባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity