+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከላፍቶ ድልድይ ወደ ጎፋ መብራት ሀይል የሚወስደው መንገድ የጥገና ስራው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከላፍቶ ወደ ጎፋ መብራት የሚወስደው መንገድ የጥገና ሥራ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አደረገ፡፡

በአካባቢው ከመኖሪያ ቤቶች እና ድርጅቶች በሚወጣ የፍሳሽ ቆሻሻ የድሬነጅ መስመር በመዝጋቱ ወደ አስፋለት የሚፈሰው የፍሳሽ ቆሻሻ መንገዱ ለብልሽት ለመዳረጉ ዋና መንስኤ ሆኖ ቆይቷል፡፡

በተጨማሪም ከተለያዩ አካባቢዎች አፈር ጭነው በሚመጡ ገልባጭ በመኪናዎች መንገድ ዳር በሚደፋ አፈር እና የመኪና እጥበት መንገዱን ለብልሽት ከመዳረጉም በላይ ለትራፊክ እንቅስቃሴ መስተጓጎል መንስኤ ሆኖ ቆይቷል፡፡

የጥገና ስራው ሙሉ በሙሉ የተጎዳውን አስፋልት ቆርጦ በማንሳት በመልሶ ግንባታ ደረጃ የተከናወነ ሲሆን 400 ሜትር ርዝመት እና 9ሜትር የጎን ስፋት የሸፈነ ነው፡፡ የተጠገነው መንገድ ረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ ከአስፋልት ጥገና ስራው ጎን ለጎን የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመር የግንባታ፣የፅዳት እና የማንሆል ክዳን እድሳት ስራንም ያካተተ ነው፡፡

በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች እና የድርጅት ባለቤቶች ዘመናዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት በመጠቀም የመንገድ ዳር የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመሮች ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ እንዲሁም የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት ከሚያደረሱ ህገወጥ ድርጊቶች በመቆጠብ የመንገድ መሰረተ ልማት ሳይበላሽ ረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.