የውስጥ ለውስጥ እና አቋራጭ የመንገድ ግንባታ ስራዎች
ጥር 6 ቀን 2015ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ መሠረተ ልማትን በከተማዋ ሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ከሚያከናውናቸው በርካታ የመንገድ ግንባታ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አጫጭርና አቋራጭ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአስፋልት ደረጃ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ካከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ባንቢስ ፍትህ ሚንስቴር አካባቢ ተጠቃሽ ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት የተሳለጠ ለማድረግ የውስጥ ለውስጥ እና አቋራጭ የመንገድ ግንባታ ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity