በተለምዶ አፍንጮ በር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የሚገኘዉ የድጋፍ ግንብ ጥገናዉ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ ጥር 05 ቀን 2015፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከዚህ ቀደም የመፍርስ አደጋ አጋጥሞት የነበረዉን አፍንጮ በር አካባቢ የሚገኘዉን የድጋፍ ግንብ በመልሶ ግንባታ ደረጃ ጥገና እያከናወነ ይገኛል ፡፡
ይህ የድጋፍ ግንብ ለረጅም አመታት ጥገና ሳይደረግለት የቆየ ከመሆኑ የተነሳ የመፍረስ አደጋ ያጋጠመዉ ሲሆን ጥገናዉ መከናወኑ በአካባቢዉ ነዋሪዎች እና በመንገድ ሀብት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ጉዳት ቀድሞ ለመከላከል ያስችላል ፡፡
ድጋፍ ግንቡ 80 ሜትር ርዝመት እና 9 ሜትር ቁመት ያለዉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኮንክሪት ሙሌት ስራ ለማከናወን ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity