አያት አደባባይ አካባቢ የድሬነጅ መስመር የመልሶ ግንባታ ስራ እየተከናወነ ነው
አዲስ አበባ፣ጥር 4 ቀን 2015ዓ.ም፣- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አያት አደባባይ አካባቢ የድሬነጅ መስመር የመልሶ ግንባታ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
በአካባቢው ከመኖሪያ ቤቶች፣ከፋብሪካዎች እና ከሆቴል ቤቶች የሚወጣ የፍሳሽ ቆሻሻ የድሬነጅ መስመር በመዝጋቱ ወደ አስፋለት የሚፈሰው ፍሳሽ መንገዱ ለብልሽት ዳርጎታል፡፡
ባለስልጣኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የድሬነጅ መስመር ግንባታ እና የፅዳት ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ የድሬነጅ መስመር መልሶ ግንባታ ስራው ሲጠናቀቅ መንገዱን ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ለማድረግ የአስፋልት ጥገና ስራው የሚከናወን ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በያዝነው ሳምንት የድሬነጅ መስመር ግንባታ እና ፅዳት ካከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል አርባ አንድ እየሱስ ፣ ቤቴል – አለም ባንክ፣ጀሞ2 እና ለቡ ሙዚቃ ሰፈር እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity