አያት ለሚኩራ ክፍለ ከተማ አካባቢ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል
አዲስ አበባ፣ ጥር 04 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የአክሰስ መንገድ በመገንባት የመንገድ መሠረተ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረተ ልማትን በከተማዋ ሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ከሚያከናውናቸው በርካታ የመንገድ ግንባታ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው አጫጭርና አቋራጭ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ስራ አንዱ ነው፡፡
የመንገድ ግንባታ ስራው አዳዲስ የመኖሪያ መንደሮች እና የመንገድ መሠረተ ልማት ያልተሟላባቸውን አካባቢዎች ትኩረት የሰጠ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ደረጃ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙባቸው አካባቢዎች ውስጥ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ አያት አካባቢ የሚጠቀስ ነው፡፡ መንገዱ አጠቃላይ 250 ሜትር ርዝመት እና 12 ሜትር የጎን ስፋት የሚሸፍን ነው፡፡
ይህ የመንገድ የግንባታ ሲጠናቀቅ በየአካባቢው ያለውን የመንገድ መሠረተ ልማት ችግር ከመቅረፍ ባለፈ ለአካባቢው ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማሳደግ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity