+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የበሻሌ ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ የአስፋልት የማልበስ ስራው እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከ 324.3 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የበሻሌ ኮንዶሚኒየም የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን እያስገነባ ይገኛል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የካቲት ወር 2013 ዓ.ም ላይ የተጀመ ሲሆን 3.5 ኪ.ሜ ርዝመትና ከ15 እስከ 20 ሜትር የሚደርስ የጎን ስፋት አለው፡፡

አሁን ላይ 1.6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል አስፋልት የማልበስ ስራ ተጠናቆ፤ ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ፊዚካል አፈፃፀም 50 በመቶ በላይ ደርሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከወሰን ማስከበር ሥራው በተያዘለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ ግንባታው በታሰበው ፍጥነት እንዳይከናወን ተፅእኖ አሳድሯል፡፡

የመንገዱን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው ጥላሁን አበበ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ጎጎት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቂ የመንገድ መሰረተ ልማት እንዲኖራቸውና የኗሪዎችንም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በበጀት ዓመቱ 19.20 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የመንገድ የመሰረተ ልማት ለመገንባት እቅድ ይዞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.