+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል?

በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል ::

ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው ?

👉 ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችን በተንጣለለ ስፍራ ላይ ቢያሳርፍም 80 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ከ4ሺህ በላይ በሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና ባሸበረቁ አበቦች የተሸፈነ ስፍራ በመሆኑ አረንጓዴነቱ ጎልቶ ይታያል።

👉 ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

👉 የአትክልት ስፍራዎቹ ጎብኚዎች አረፍ ብለው ንፋስ የሚቀበሉባቸው ምቹ መቀመጫዎችን እንዲሁም በጥበብ ስራዎች የሚዝናኑባቸውን የስነ ጥበብና የመዝናኛ ቦታዎችን የያዙ ናቸው።

👉 ትልቁ ህንጻ ከ15ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

👉 ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ነው።

EBC

Comments are closed.