+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ ጥገና ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል

መስከረም 20 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በብልሽት ምክንያት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ መንገዶችን በመለየት መጠነ ሰፊ የጥገና ስራዎች እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ረጅም ጊዜ በማገልገልና የክረምቱን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ለብልሽት የተዳረጉና ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ መንገዶችን በመለየት እንደብልሽት መጠናቸው ቀላልና በመልሶ ግንባታ ደረጃ የአስፋልት ጥገና ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በያዝነው ሳምንት የመንገድ ጥገና እየተከናወነ ከሚገኝባቸው አካባቢዎች መካከል ከአራዳ ህንፃ-ቴዎድሮስ አደባባይ-ለገሀር፣ ፈረንሳይ ጉራራ፣ ቦሌ ስካይ ላይት ሆቴል፣ ከጎተራ ማሳለጫ-ቃሊት አደባባይ፣ ቦሌ ሚካኤል ቀለበት መንገድ እና ሌሎችም አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡

በቀጣይም የመንገድ ጥገና ስራውን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል የአስፋልት መንገዶችን ደረጃ በማሻሻል የትፊራክ ፍሰቱ የተሳለጠ ለማድረግ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/

Comments are closed.