2015 በጀት ዓመት 611.6 ኪ.ሜ የጥገና ስራዎችን ለማከናወን ታቅዷል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13 ቀን 2015 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2015 በጀት ዓመት 611.6 ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ስራዎችን ለማከናወን እቅድ ይዟል፡፡
ባለስልጣኑ አሁን ላይ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ በክረምቱ ከባድ ዝናብና በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ መንገዶችን የመለየት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 110 ኪ.ሜ የአስፋልት፣20 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 80 ኪ.ሜ የኮብል፣341.29 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና፣ 50 ኪ.ሜ ነባርና አዳዲስ መንገዶችን የትራፊክ ቀለም ቅብ ስራዎች፣ 10 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድና የከርቨ ስቶን ጥገና እንዲሁም 0.3 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ የጥገና ስራዎችን ለማከናወን አቅዷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በቁጥር 29 ድልድዮች እና 14 ሺ የሚደርሱ የመንገድ ዳር መብራቶች አምፖል ጥገና እና አምፖል መቀየር ስራዎች የዕቅዱ አካል ሆነው ተካተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads
ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity
ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡ https://www.instagram.com/addisababaroads/
