“ልዩ ምስጋና ለቄራና አካባቢው ማህበረሰብ !!
መንገዱ ክረምት ከበጋ ሲሰራ የተለያዩ ችግሮችን በትዕግስት አብራችሁን ያለፋችሁ ፣ መንገዱ የሚሰራባቸውን እቃዎች በመጠበቅ አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ የቄራ አካባቢ ማህበረሰብን እና የልማት ተነሺዎችን እጅግ እናመሰግናቹሃለን።
ዛሬ ለውጡን ስታዩ ‘እንኳንም ታገስን’ እንዳላችሁ እናምናለን። አሁንም አካባቢያችሁን ልዩ ውበት ያላበሰውን ይህንን ዘመናዊ መንገድ እንደ አይናችሁ ብሌን በመጠበቅና በመንከባከብ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እላለሁ ፤
ከአክብሮት ጋር !!”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ


Previous Post
Next Post
Users Today : 2
Users Last 7 days : 271
Users Last 30 days : 1023