በአይነቱ ልዩ የሆነው የፑሽኪን – ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት በነገው እለት ነሃሴ 9 ቀን ለምረቃ ይበቃል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ ስሟንና አለም አቀፍ ደረጃዋን የሚመጥን፤ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ ብሎም የከተማዋን የትራንስፖርት ችግሮች ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ከነዚህ ውስጥ በከተማዋ የመንገድ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው ዘመናዊና ዘመኑ የደረሰበትን መንገድ ስራ ጥበብ የታየበት ከአሌክሳደር ፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ማሳለጫ ድረስ ያለውን የመንገድ ፕሮጀክት በነገው እለት ነሃሴ 9 ቀን አጠናቆ ያስመርቃል፡፡
ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ የህዝባችንን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን!!!
መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን!!
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads