+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በእግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ እቃ ያስቀመጡ ድርጅቶች የግንባታ ፈቃዳቸዉ ሊሰረዝ ይችላል ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በእግረኛ መንገድ ላይ የግንባታ እቃዎች ያስቀመጡ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ለአንድም ቀን ይሁን ይህ ማድረግ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታዉቋል፡፡

ያለ ይዞታቸው የእግረኛ መንገድን የሚያጨናንቁ ድርጅቶች መኖራቸውን ደርሸበታለሁ ያለዉ ባለስልጣኑ፣ በአስቸኳይ እንዲያነሱ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በባለስልጣኑ የግንባታ ክትትል እና ቁጥጥር ዳሬክትር አቶ ሙሉጌታ ሊክዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከተሰጣቸው የግንባታ ቦታ ውጪ የሚጠቀሙና የግንባታ እቃ የሚያስቀመጡ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ ነግረዉናል፡፡

ለእግረኛ ተብሎ በተሰራ ቦታ ላይ በማን አለብኝነት የግንባታ እቃዎች ማለትም አሸዋ፣ድንጋይ፣ ፌሮ እና ሌሎችም እቃዎች ያስቀመጡ ድርቶች የግንባታ ፈቃዳቸዉን እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ሊወሰድባቸዉ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

በእግረኛ መንገዶች ላይ የሚቀመጡ የግንባታ ግብዓቶች ዓይነስውራን እና አካል ጉዳታኞች ለከፍተኛ ችግር እንዲጋለጡ እያደረጉ መሆናቸዉንም ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

Comments are closed.