+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ የጎርፍ ስጋትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመንገድ ዳር የሚገኙት የውሃ ፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮችና ድልድዮች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ በጋው ወራት ሲያከናውናቸው ከነበሩት የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ሥራዎች በተጨማሪ የክረምቱን መግባት ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉ የጎርፍ ስጋቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የፅዳትና የጥገና ስራዎች እየተከናወኑ ከሚገኙባቸው ቦታዎች መካከል ከካሳንችስ መብራት እስከ ባምቢስ፣ ከካሳንችስ ሀናን ዳቦ ቤት – ከካሳንችስ መብራት፣ ፈረንሳይ 41 ኢየሱስ፣ ከጀርመን አደባባይ ጎፋ ድልድይ፣ ቱሉ ድምቱ ኮንዶሚኒየም፣ ከጀርመን አደባባይ ለቡ መብራት፣ አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር፣ ልደታ ፀበል፣ ጎፋ መብራት ኮንዶሚኒየም እና ሌሎችም አካባቢዎች ይጠቀሳሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.