+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣኑ ሠራተኞች የዕቅድ እና በጀት ጥያቄ አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወሰዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች የዕቅድ እና በጀት ጥያቄ አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወሰዱ፡፡በባለስለጣን መስሪያ ቤቱ ዕቅድ፣ በጀትና ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀው ይህ መድረክ በበጀት ዝግጅት ላይ ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው፡፡ ከመድረኩ እንደተገለፀው ወቅቱ ለቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድና የበጀት ዝግጅት የሚደረግበት ጊዜ እንደመሆኑ ከዚህ በፊት በበጀት ዝግጅት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የተናበበ እና የጠራ እቅድ ዝግጅት እንዲደረግ የሚረዳ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የዕቅድ አዘገጃጀት ሂደት፣ በ2014 በጀት ዝግጅት ያጋጠሙ ችግሮች እና በ2015 በጀት ዓመት በጀት ዝግጅት ወቅት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጐባቸዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ቴሌግራም: https://t.me/AddisRoads

ፌስ ቡክ : https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር : https://twitter.com/AbabaCity

Comments are closed.