+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ ዳር የውሃ ፍሳሽ መስመር ጽዳትና ጥገና በመከናወን ላይ ነው

መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በክረምት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ታሳቢ በማድረግ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ ዳር የውሃ ፍሳሽ መስመር ጽዳት፣ ጥገና እና መልሶ ግንባታ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

የድሬኔጅ መስመር ጥገና ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል፤ ላፍቶ 58፣ አየር ጤና አደባባይ፣ ከጀሞ ሚካኤል – ዊንኔት፣ መርካቶ ከራጉኤል ቤተ ክርስቲያን – ዱባይ ተራ፣ ከሰሚት – 72፣ ቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

Comments are closed.