ከየካቲት 23 ወደ ጀሞ 2 የሚወስድ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፤ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 2 ከየካቲት 23 ሆቴል ወደ ጀሞ 2 የሚያደርስ አቋራጭ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ጀመረ፡፡
ቀደም ሲል ተገንብቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ነባሩ መንገድ የተጎዳ በመሆኑ፤ 940 ሜትር ርዝመት እና እግረኛ መንገድን ጨምሮ 20 ሜትር የጎን ስፋት ያለው መንገድ በአዲስ መልክ እየተገነባ ነው፡፡
አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ በመከናነወን ላይ ሲሆን፤ ግንባታ ሥራው መኮንን አንለይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ሆኖስ ቢውሊዲንግ ኮንስትራክሽን በተባሉ ማህበራት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ የአስፋልትና ተያያዥ ቀጣይ ስራዎች በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል የሚከናወኑ ይሆናል፡፡
የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ፤ ከካራ ቆሬ እና አካባቢው ወደ ጀሞ 2 ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች አቋራጭ መንገድ በመሆን፣ በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት የሚያቀላጠፍ ይሆናል፡፡


Previous Post
Next Post
Users Today : 15
Users Last 7 days : 339
Users Last 30 days : 1255