+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በአንድ ጀንበር 714.7 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ከዕቅድ በላይ መሳካቱን ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለፁ ።

በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 714.7 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል ፡፡

አጠቃላይ 29.7 ሚሊዮን ሕዝብ እንደተሳተፈ የተናገሩት ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ፤ የዛሬው ቀን የኢትዮጵያ ሕዝብ በሕብረት ታሪክ የሠራበት ዕለት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መርሐ ግብሩ እንዲሳካ በማስተባበር እና በመሳተፍ ታሪክ የሰሩ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አመስግነዋል፡፡

Comments are closed.