በጎማቸው ጭቃ በመያዝ መንገድ ያበላሹ 14 አሽከርካሪዎች ተቀጡ!
በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በላከው መረጃ እንዳስታወቀው በክፍለከተማው በተሽከርካሪ መንገዶች ላይ ተረፈ ምርንትን መንገድ ላይ በማንጠባጠብ እና በጎማ ጭቃ በማበላሸት ለፍሰት እንቅፋት የፈጠሩ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ 14 አሸከርካሪዎችን መቅጣቱን አስታውቋል።
መንገዱ የተበላሸው በቦሌ አየር መንገድ ጀርባ፣ ቡልቡላ፣ ሪፌንቲ አደባባይና ቦሌ ሆምስ አካባቢዎች ሲሆን ያበላሹትን መንገድ እንዲያጥቡ መደረጉንም መረጃው ጠቁሟል።
መሰል ቁጥጥሩም በኮንስትራክሽን አካባቢዎች በጎሮ፣ አርሴማ ጸበልና ወረገኑ አካባቢ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል።
