+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ 417 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ ፅዳትና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ በርካታ አካባቢዎች ላይ በዝናብ ወቅት ሊከሰት የሚችል የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል የሚያስችል የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና የጥገና ስራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡

ባለሥልጣኑ በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ተከታታይ 9 ወራት ውስጥ 432.8 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመሮችን የፅዳት ስራዎችን ለማከናወን አቅዶ 417.3 ኪሎ ሜትር ለማከናወን ችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ባለስልጣኑ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት ደርሶባቸው አገልግሎት የማይሰጡ 4.51 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ የድሬኔጅ መስመሮችን በመለየት የዕድሳትና የጥገና ስራዎችን አከናውኗል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የጎርፍ አደጋ ስጋት ሊከሰትባቸው ይችላሉ ተብለው በባለድርሻ አካላትና በህብረተሰቡ ጥቆማ ቀርበው የተለዩ ቦታዎች ላይ ከ 3.14 ኪሎ ሜትር በላይ አዲስ የድሬኔጅ መስመር ግንባታም ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር (X) ፡- https://twitter.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.