+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ወርቃማው ሰኞ

ሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የሣምንቱን ሥራ ቀናት በተነቃቃ እና ብርቱ የሥራ መንፈስ ለመጀመር፤ ዛሬ ማለዳ የወርቃማውን ሰኞ መርሃ ግብር በዋናው መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ በጋራ አከናውነናል፡፡

ፕሮግራሙ የሠራተኛውን አንድነትና የሥራ ትብብር የሚያጠናክር፣ የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥን የሚያሳድግ እና የተጀመረውን ጠንካራ የሥራ ባህል የመገንባት እንቅስቃሴ የሚያጎለብት መድረክ በመሆኑ ወደፊትም በሁሉም የተቋማችን የሥራ ክፍሎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በእያንዳንዱ ሰው ህይወት ዙሪያ ሌሎች ተሞክሮ ሊወስዱበት የሚያስችል ቢያንስ የአንድ ውድ መፅሐፍ ገጽ አለ፡፡

በመሆኑም የወርቃማውን ሰኞ መድረክ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፤ ተቋማዊ የመፈፀም አቅማችንን ለማሳደግ እና አገልግሎት አሰጣጣችን የህብረተሰቡን እርካታ ይበልጥ የሚያረጋግጥ እንዲሆን ለማስቻል እንጠቀምበታለን፡፡

ለሁላችሁም በያላችሁበት መልካም የሥራ ሣምንት ይሁንላችሁ!

Comments are closed.