በመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከጠብታ አምቡላንስ ጋር በመተባበር 70 ለሚሆኑ ሠራተኞ በመጀመሪያ ህክምና ዕርዳታ አሰጣጥ ዙሪያ የሁለት ቀን ቆይታ ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የባለስልጣኑ የስልጠና ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መስፍን በተቋሙ ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች፣ የሴፍቲ ኦፊሰሮች፣ እና በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ለተሰማሩ ሠራተኞች በመጀመሪያ ደረጃ የህክምና አሰጣጥ ወቅት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች በንድፈ ሀሳብና በተግባር የታገዘ የ2 ቀን ስልጠና መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡
ስልጠናውን ከሰጡት የጠብታ አምቡላስ የጤና ባለሙያዎች መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሪት መቅደስ ስዩም በበኩላቸው በስራ እና በተለያዩ ቦታዎች ድንገተኛ አደጋ በሚያጋጥምበት ወቅት የራስን ደህነነት አስጠብቆ ለተጎጂዎች በእውቀት ላይ የተመሰረተ የመጀመሪያ ህክምና ዕርዳት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ የሠራተኞችን የመፈፀም ብቃት ለማጎልበት የሚያስችሉ በርካታ ሙያዊ ስልጠናዎችንም አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
