+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሴት ሠራተኞች አየር ኃይልን ጎበኙ።

የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሴት ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የኢፌዴሪ አየር ኃይልን ጎብኝተዋል፡፡

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮለኔል መኳንንት ደሳለኝ፤ የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበር ሂደት ጉልህ ሚና እያበረከተ የሚገኘው የሀገሪቱ አየር ኃይል ከ89 ዓመት በፊት ስራውን እንደተመሠረተ አስታውሰው፤ አሁን ላይ ተቋሙ የተጣለበትን ከፍተኛ ተልዕኮ በብቃት መወጣት ይችል ዘንድ በሰው ኃይል፣ በመሰረተ ልማት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየተጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

የባለስልጣኑ ሴት ሠራተኞች በአየር ኃይል ቅጥር ግቢ በነበራቸው ቆይታ የአቪዬሽኑን የጥገና ማዕከል፣ የበረራ እና የስልጠና ማዕከል፣ የአካባቢ ልማት እና የምድረ-ግቢ ማስዋብ ሥራዎችን እንዲሁም የከተማ ግብርና ልማት ስራዎችን እና የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን የጎበኙ ሲሆን፤ ከሴት የጦር አውሮኘላን አብራሪ ተማሪዎችም ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በተቋሙ የጦር አውሮኘላን አብራሪነት ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙት ሲኒየር ካዴት አያንቱ ካሳ እና ሃዊ ግርማ ስራው በሴት ያልተለመደ ቢሆንም፣ በፍቅርና በትጋት ከተሰራ ሴቶች በተለያዩ መስኮች ከወንዶች እኩል ተሰልፈው መስራት እንደሚችሉ በተግባር ማሳየት በመቻላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ለጉብኝቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል፡፡

የጉብኝቱ ተሣታፊዎች በበኩላቸው እድሉን አግኝተው የኢፌዴሪ አየር ኃይልን በመጎብኘታቸው ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው፣ በቆይታቸው በርካታ ጠቃሚ ልምዶችን መቅሰማቸውን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.