የኮሪደር ልማቱ ዘመናዊ የከተማ ገፅታ ከመፍጠር ባሻገር፡ በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በተቀናጀ አሠራር ለመከላከል የሚያስችል ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል”
ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም፡- በመዲናዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት፤ የትራንስፖርት አማራጮችን በማስፋት፣ ምቹና ሁሉን አቀፍ የመንገድ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ከማስቻሉም ባሻገር፤ በመንገድ ሀብት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በመከላከል በኩል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ ገልፀዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱ ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር ጀምሮ በርካታ መልካም አጋጣሚዎችን ይዞ የመጣ ነው ያሉት ኢንጂነር ሙህዲን፤ በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ከጉዳት ከመካከል እና በተናበበ የመሠረተ-ልማት አቅርቦት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ቅንጅታዊ አሠራርን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ
