+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ ለተቀጠሩ የምህንድስና ባለሙያዎች ሥልጠና እየተሰጠ ነው

የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር አዲስ ለተጠቀሩ ጁኒየር የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ኃብትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ተ/ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ገብሬ፤ ሥልጠናው የመንገድ መሠረተ ልማት ዘርፍ ስራዎችን በብቃት ለማከናወን ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው፤ ወደ ተቋሙ የተቀላቀሉት ጁኒየር የምህንድስና ባለሙያዎች በሥልጠናው የሚቀስሙትን እውቀት በስራ ላይ በማዋል የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባብ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ለተከታታይ 10 ቀናት የሚሰጠው በዚህ ሥልጠና ላይ 80 የሚሆኑ የምህንድስና ባለሙያዎች እየተካፈሉ ሲሆን፤ ስልጠናው በምህንድስና ግዢና ኮንትራት አስተዳደር፣ በመንገድ ግንባታ ጥራትና ደህንነት ማኔጅመንት፣ በግንባታ ሙያ ሥነ-ምግባር እና በመንገድ ሃብት አስተዳደር ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፤ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱን ተልዕኮ፣ የሰራተኛ መብትና ግዴታዎችን እንዲሁም የተቋሙን የአሰራር መመሪያዎች መሠረት ያደረገ ገለፃን ያካተተ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ: https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.