የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል እየተከናወነ የሚገኘው የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና የጥገና ስራ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የከተማዋን የመነገድ ደህንነት ለማረጋገጥ እና በዝናብ ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመከላከል የሚያስችል የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና እድሳት ስራዎች ከወዲሁ እያከናወነ ይገኛል፡፡
አሁኑ ላይ የማንሆል ክዳን፣ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና የጥገና ስራዎች በስፋት እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ሲ.ኤም.ሲ ፀሐይ ሪል እስቴት አካባቢ፣ ጉለሌ ወረዳ አራት ሳሙና ፋብሪካ አካባቢ፣ መገናኛ ለም ሆቴል፣ ላምበረት እና ካራ አካባቢዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በተያያዘም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት 388 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ስራ ለማከናወኑ ይታወሳል፡፡
