+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት ያሳካቸዉ የፕሮጀክቶች አፈፀፀም በተመለከተ፤-

👉ፕሮጀክቶች በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ ባህልን በማዳበር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን መሰረተ-ልማቶች፤ዲዛይንና ግንባታን በማከናወን የህበረተሰቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባቀድነው መሰረት 217 ግንባታዎችን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

👉ለአብነት፡-ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ፣ ት/ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የአስተዳደር ህንፃዎች ፣የተለያዩ ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ አቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ምዕራፍ አንድ፣ የሼድ ግንባታዎችና የየካቲት 12ሆስፒታል እድሳት እና መሰል ፕሮጀክቶች ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቀዋል፡፡

👉በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኙትም፤-ሃይሌ ጋርመንት የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል ግንባታ 98% ፣የህፃናትና ወጣቶቸ ቴያትር ምዕራፍ ሶስት 81.25 %፤ራስ ደስታ ሆስፒታል B+ጂ+5 ህንፃ የእድሳት ስራ 87.5% ፣ኮልፌ አጠቃላይ ሆስፒታል 82%፣ ላፍቶ ሆስፒታል 80%፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 85%፣ ዘውዲቱ ሆስፒታል 71% ግንባታቸዉን ማድረስ ተችሏል፡፤

👉ከሜጋ ፕሮጀክቶች አንፃር የአዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኤግዝብሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታዉን ማጠናቀቅ ተችሏል።

👉ይህ ግዙፍ ማዕከል ከተማችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ተመራጭና ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የከተማዋን ብሎም የሀገራችንን ገፅታ በመቀየር ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ይሆናል።

👉እንዲሁም 13 ነባር ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን ለአብነትም የትራንስፖርት ቢሮ ሕንፃ ግንባታ 67.88%፤ አዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ግንባታ 76.11%፤ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪያ ክላስተር ግንባታ ሎት 3 / 93.6%፤ ሎት 153 % የካ 2 G+5 መኪና ማቆሚያ ግንባታ 97.5% ተጠቃሽናቸዉ፡፡

👉 ፕሮጀክቶቹ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በከፍተኛ ሁኔታ የከተማውንና የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የሚያቃሉ በመሆናቸዉ ባልተጠናቀቁት ላይ በተያዘላቸው በጀትና ጊዜ ልዩ ትኩረት በመስጠት በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.