+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከአስኮ ታክሲ ተርሚናል- ሚኪላንድ ኮንዶሚኒየም የሚወስደው መንገድ የማስፋፍያ ስራ እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአስኮ ታክሲ ተርሚናል ወደ ሚኪላንድ ኮንዶሚኒየም የሚወስደው መንገድ የትራፊክ ፍሰት ለማሻሻል የማስፋፊያ ስራ በማከናወን ላይ ነው፡፡

የማስፋፊያ ስራው በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የራስ ኃይል እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ አጠቃላይ የመንገዱ ርዝመት 875 ሜትር የሚሸፍን ነው፡፡

የመንገድ ማስፋፊያ ስራው በተያዘው በጀት ዓመት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የትቦ ቀበራ፣ የሙሌትና ተያያዥ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ቀደም ሲል የነበረው መንገዱ ስፋት 7 ሜትር ሲሆን፤ አሁን ላይ እየተከናወነ ባለው የማስፋፊያ ስራ የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ወደ 16 ሜትር የጎን ስፋት ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የመንገድ ማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

Comments are closed.