+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለ38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ድምቀት መንገዶችን የማስዋብ እና የጥገና ስራ ተከናውኗል

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን 38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ድምቀት እንግዶች በሚተላለፉባቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ የጥገና እና የማስዋብ ስራዎችን በስፋት አከናውኗል፡፡

የመንገድ ጥገና እና ማስዋብ ሥራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ከአራት ኪሎ – እስጢፋኖስ፣ ከእስጢፋኖስ – ቦሌ፣ ከቸርችል ጎዳና – ሜክሲኮ- አፍሪካ ህብረት፣ ከእስጢፋኖስ – በለገሃር – ሜክሲኮ፣ ከሂልተን – ካሳንቺስ እና አካባቢው ይገኙበታል።

በእነዚህ እና በሌሎች አካባቢዎች ከተከናወኑ የጥገና ስራዎች መካከል የአስፋልት እና የእግረኛ መንገዶች ጥገና፣ የከርቭ ስቶን ግንባታና ጥገና፣ መንገዶችን የማጽዳት እና የማስዋብ ስራዎች እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት አካባቢ 2 ሺህ 400 ካሬ ስፋት ያለው የመኪና ማቆሚያ ግንባታ ስራዎች ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ፤ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የመንገድ መሠረተ-ልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ብቻ በአጠቃላይ 611 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ማከናወኑ ይታወሳል

Comments are closed.