+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

አዲስ አበባ የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሳታፊዎችን ወደ ምድረ ቀደምት፣ የፓን አፍሪካኒዝም መነሻ እንዲሁም የጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት ተምሳሌትና ኩራት ወደ ሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁ ትላለች።

አዲስ አበባ እንደ ስሟ ዉብ እና አዲስ ሆና በድንቅ የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት ልታስተናግዳችሁ ተዘጋጅታለች።

ውድ የከተማችን ነዋሪዎችም በተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንግዶችን ተቀብላችሁ እንደምታስተናግዱ እምነቴ የፀና ነዉ።

እንግዶቻችን የሚኖራችሁ ቆይታ ፍጹም ስኬታማ እና አስደሳች እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያዊ ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.