ዝምታው ይሰበር!
የዜጎች ደህንነት – ስጋት ሳያርፍበት፣
ሰውና ንብረቱ – ጉዳት ሳይደርስበት፤
የመንገድ ሃብታችን – እንዲውል ከግቡ፣
ያገባኛል ብለን – የማንቆጭበት፣
ቸልታው አልበዛም – የተፋዘዝንበት?
መታገስ እርቆን – መከባበር ጠፍቶ፣
መናናቅ ክፋቱ – እኔነቱ በዝቶ፤
የየለቱ ክስተት – አደጋ ሆነና፣
ሰቆቃና ዋይታው – በዝቷል በጎዳና፡፡
በሠላም ወጥቶ – በሠላም ለመግባት፣
በሁላችንም ዘንድ – ያስፈልጋል ትግስት፡፡
ይልቅ እንደዋዛ – ለሚደርሰው ውድመት፣
ለአካል ጉዳቱና – ለሚጠፋው ህይወት፤
ችግር የሚፈታ – መፍትሔ ለማምጣት፣
ዝምታው ይሰበር – እንወያይበት፡፡