+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ደርሷል

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም፡- በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት 3 ወራት በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች ግጭት ምክንያት ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የመንገድ መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አጠቃላይ 85 የግጭት አደጋዎች የደረሱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 27 የሚሆኑት በቀለበት መንገድ ላይ ሲከሰቱ 58 የግጭት አደጋዎች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ ያጋጠሙ ናቸው፡

በግጭት አደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው የመንገድ መሰረተ ልማቶች መካከል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተገዝተው በምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ በተተከሉ የመንገድ መብራት ምሶሶዎች ፣ የትራፊክ ምልክቶች ፣ የአቅጣጫና ርቀት አመላካች ሰሌዳዎች ፣የእግረኛ መከላከያ አጥሮች ፣ የመንገድ ማካፈያ ግንቦች እና የማንሆል ክዳኖች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በእግረኛ መንገዶች ላይ የግንባታ ተረፈ ምርቶች ማከማቸት ፣ህገወጥ የመንገድ ላይ ንግድ እንዲሁም አሽከርካሪዎች ከግንባታ ሳይቶች ሲወጡ ጎማቸውን በአግባቡ ሳያፀዱ ወደ መንገድ በመውጣታቸው የአስፋልት መንገዱን በጭቃ እና በግንባታ ተረፈ ምርት በከፍተኛ ደረጃ በማበላሸት የመንገድ ሀብት ላይ ጉዳት እየደረሰ ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ በተሸከርካሪዎች ግጭት ምክንያት የመንገድ ሀብቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በመጠገን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እንዲያስችለው ከግጭት አድራሾችና ከሌሎች የአገልግሎቶች ክፍያዎች ተመጣጣኝ የጉዳት ካሳ ለመሰብሰብ ችሏል፡፡

በመሆኑን መንገድ የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀብት በመሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት የሁሉም ህብረተሰብ ጉዳት መሆኑን በመረዳ በእኔነት ስሜት የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል የመንገድ መሰረተ ልማቶች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ ሲል ባለስልጣኑ የዘወትር መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ

Comments are closed.