በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ497 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች ተከናውነዋል
አፈፃፀሙ ከ2016 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ 61 በመቶ ብልጫ አለው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 262 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች ለመስራት አቅዶ 497 ኪሎ ሜትር በማከናወን ከዕቅዱ በላይ ማሳካት ችሏል፡፡
በሩብ ዓመቱ ከ52 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍን ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተገነቡ መንገዶችን ጨምሮ፣ 8.7 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 2.76 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 27.45 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ መንገድ ስራዎች ይገኙበታል፡፡
በሌላም በኩል፤ ነባር የእግረኛ መንገዶችን ለማዘመን 12.1 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ የመልሶ ግንባታ ስራ ከመከናወኑም በተጨማሪ፣ 1.57 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የዝናብ ውሀ መፋሰሻ መስመር ግንባታ፣ 0.35 ኪሎ ሜትር የጋራ መኖሪያ ቤቶች የኮብል ስቶን መንገዶች የሰብ ቤዝ ዝግጅት ስራ ተካሂዷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ምክንያቶች ለብልሽት የተዳረጉ 22.16 ኪ.ሜ የአስፋልት፣ 2.27 ከ.ሜ የጠጠር፣ 0.42 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ መከለያ አጥር ስራ፣ ከ268 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ መስመሮች ፅዳት፣ 1.28 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ዕድሳትና ጥገና፣ 3.38 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ባለስልጣኑ 145.38 ኪሎ ሜትር የሚሆን በአዲስና ነባር የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የእግረኛ መከላከያ አጥር የቀለም ቅብ ስራ እና 1.51 ኪሎ ሜትር ለሌሎች የመሰረተ ልማት የማሻሽያ ስራዎች ሲባል የተቆረጡ መንገዶች መልሶ በመጠገን፤ በድምሩም 444.75 ኪሎ ሜትር የጥገና ስራዎችን በሩብ ዓመቱ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡
በሌላም በኩል፤ 2 ሺህ 928 የመንገድ መብራት ፖል እና አምፖል ጥገና ስራዎች በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የሚካተቱ የመንገድ ጥገና ተግባራት ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ
ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity
ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/
ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads
ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et
ለማንኛውም ጥቆማ ፡- 8267 ነጻ የስልክ መስመር ይጠቀሙ