+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ተቋሙ ለሚደግፋቸው 50 ህፃናት የአዲስ ዓመት የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም፡- “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው የኅብር ቀን፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በቋሚነት ለሚደግፋቸው 50 ህፃናት የአዲስ ዓመት በዓል መዋያ ድጋፍና በ2016 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የተቋሙ ሠራተኞች እውቅና ተሰጠ።

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በየወሩ በቋሚነት ከደመወዛቸው በማዋጣት ለሚደግፏቸው ለችግር ለተጋለጡ ሃምሳ ህፃናት ከባለስልጣኑ ሰራተኞች እና ከባለድርሻ አካላት በተሰበሰበ 220 ሺህ ብር የ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል መዋያ ለእያንዳንዳቸው 2800 ብር፣ 5 ኪሎ ግራም ዱቄት እና 5 ሊትር ዘይት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ፤ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያደረጉት አርዓያነት ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ የበጎነት ተግባር ወደፊትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው የህፃናት ወላጆችና አሳዳጊዎች በበኩላቸው ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በየጊዜው ለሚያደርግላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመርሀ ግብሩ ላይ በ2016 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የተቋሙ ሠራተኞችና የስራ ክፍሎች እውቅና ተሰቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ ፡- https://www.aacra.gov.et

Comments are closed.