የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ ላበረከተው የላቀ አስተዋፆኦ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እውቅና ተሰጥቶታል።
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በኮሪደር ልማቱ
የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እንዲወጣና ለዚህ እውቅና እንዲበቃ የበኩላችሁን ድርሻ በትጋት ለተወጣችሁ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አመራርና ሠራተኞች በሙሉ በያላችሁበት ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
እንደ ተቋም የተሰጠን ይህ ምስጋናና ዕውቅና ተጨማሪ አቅምና ስንቅ ሆኖን፤ የመንገድ መሠረተ-ልማት ግንባታ ዋነኛ ተልዕኳችን አንዱ አካል በሆነው በክፍል ሁለት የኮሪደር ልማት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የከተማችንን ነዋሪዎች እርካታ ለማረጋገጥና የአዲስ አበባን ገፅታ ይበልጥ ለማዘመን እንዘጋጅ!
የተሻለ መንገድ፣ ለተሻለች አዲስ አበባ!