+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ ያልሆኑ ቦታዎች ፈጣን ማስተካከያ እንዲደረግባቸው የሥራ መመሪያ ተሰጠ

አዲሱ የባለሥልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተለያዩ የሥራ ክፍል መሪዎችን አነጋግረዋል

ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ፈጣን ምላሽ በሚጠይቁ የመንገድ ጥገና ሥራዎች ላይ ከሚመለከታቸው የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በክረምቱ ዝናብ ሳቢያ በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ መስተጓጎል የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን በቀጣዮቹ 15 ቀናት ማስተካከል ይቻል ዘንድ፤ የመንገድ ሀብት አስተዳደርና የኦፕሬሽን ዘርፎች በቅንጅት ሊፈፅሟቸው በሚገቡ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ትኩረት በማድርግ ዛሬ ከቀትር በፊት የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ ቀናትም፤ ወቅታዊ ሥራዎች በፍጥነት እንዲፈፀሙና የ2017 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎችን ከወዲሁ ማጠናቀቅ የሚያስችሉ ተከታታይ ውይይቶች በተለያዩ ዘርፎች ስር ከተደራጁ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍል መሪዎች ጋር ይካሄዳል፡፡

በሌላም በኩል፤ የባለሥልጣን መስሪያቤቱን የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ለመፈፀም የሚያስችሉ የተለያዩ ኮሚቴዎች ተደራጅተው ወደ ተግባር እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.