+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ፈጣን ምላሽ ለሚጠይቁ አደጋዎች ምላሽ የሚሰጥ ግብረ ኃይል ተቋቋመ

ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በክረምቱ ወቅት ሊከሰቱ ለሚችሉ የጎርፍ አደጋ ስጋቶች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ግብረ-ኃይል አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከመንገድ ጋር በተያያዘ ለጎርፍ አደጋ አጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት በበጋው ወራት የተለያዩ የመፍትሔ እርምጃዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።

በዚህም መሠረት በ2016 በጀት ዓመት ብቻ ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና ማከናወኑ ይታወሳል።

አሁን ላይ በክረምቱ ወራት ሊከሰት የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ታሳቢ ያደረገ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ቅድመ-ዝግጅት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በዚህ ሳምንት እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭቱ እየተጠናከረ እንደሚሔድ ገልጿል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚገኙ ክፍት የመንገድ ዳር ውሃ መፋሰሻ መስመሮችን በማፅዳትና ወደ ድሬኔጅ መስመሮች ቆሻሻ ባለመጣል የጎርፍ አደጋ መከላከል ሥራውን እንዲያግዝ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን ይቀላቀሉ

ፌስ ቡክ :- https://www.facebook.com/AbabaCity

ቴሌግራም:- https://t.me/AddisRoads

ትዊተር :- https://twitter.com/AbabaCity

ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/addisababaroads/

ዩቱዩብ:- https://www.youtube.com/@addisababacityroadsauthori1369

ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@addisababaroads

Comments are closed.