+251 11371 2982 aacracom@gmail.com

ከሁሉም በፊት የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!

ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ ማጠናቀቅን ባህል ያደረገችው አዲስ አበባ ዛሬም ተጨማሪ ብስራት ለነዋሪዎቿ እነሆ ብላለች!!

ከአራት ኪሎ ፣ ቀበና እስከ ኬኒያ ኤምባሲ ያለው መንገድ በኮሪደር ልማት ስራችን አልምተን እና አስውበን ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት እንዲውል ክፍት ያደረግን ሲሆን ይህም ሶስተኛው ያጠናቀቅነው ስራችን ነው::

አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ አበባ እና ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ በማድረግ ዓለም-አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር መንዝረን ምቹ የእግረኛ መንገዶችን ፣ የሞተር አልባ(ብስክሌት) መንገዶች ፣ ምቹ የታክሲ/ባስ ማውረጃና መጫኛ ስፍራዎችን ፣ የመኪና ፓርኪንጎችን ፣ አረንጏዴ ስፍራዎችን ፣ የመንገድ ዳርቻ ማረፊያ መቀመጫዎችን ፣ የህዝብ መናፈሻዎችን ፣ የከተማዋን ስታንዳርድ የሚመጥኑ መብራቶችንና ፉዋፉዋቴዎችን ባጠረ ጊዜ ገንብተን አዲስ አበባ ከተማን 24 ሰዓት የደራችና ከቆሻሻ በእጅጉ እየጸዳች ያለች ከተማ አድርገናል::

የኮሪደር ልማት ስራን የሰራንባቸው አካባቢዎች የተሳለጠ ትራንስፖርትና ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ከመፍጠር በተጨማሪ ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠሩ እና 24/7 በመስራት አዲስ የስራ ባህል በማስተዋወቅ ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን አለምአቀፍ ተወዳዳሪ የሆነች ዘመናዊ ከተማ የማድረግ ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን::

ይህ የኮሪደር ስራ እውን እንዲሆን ፕሮጀክቶቹን በመከታተል የደገፋችሁ፣ በትጋት ያስተባበራችሁ፣ ከሁሉ በላይ በእልህ አስጨራሽ ሁኔታዎች ሁሉ ውስጥ በትዕግስት ከጎናችን በመቆም የደገፋችሁን በተለይም መሬታችሁን ለልማት የለቀቃችሁ ፣ ከመኖሪያ አካባቢያችሁ ያዘዋወርናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች በቀና ትብብራችሁ እና ከራስ በላይ ለትውልድ ዘላቂ ልማት በማሰብ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድናሳካው አቅም ስለሆናችሁን እጅግ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: አዲስ አበባ ታመሰግናችኃለች::

በኮሪደር ልማት ያጌጠች በዲጂታል አገልግሎት የዘመነች ለመኖር ምቹ ከተማ -አዲስ አበባ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Comments are closed.